የመምህራን ኅብረት

የመምህራኑ ኅብረት ለሊጎኔር ሚኒስትሪስ የተለዩ ስጦታዎችን፣ ሰፋ ያሉ ተሞክሮዎችንና የሚያግዙ ዕይታዎችን ያመጣል። ለተመሠረትንበት ዐላማ ታማኝ እንድንሆን በማገዝ፣ እንዲሁም የወደፊቱን አገልግሎታችንን በመምራትና በግልጽ በማስቀመጥ ሊጎኔርን ያገለግላሉ። ዶ/ር አር. ሲ. ስፕሮልና ቦርዱ ይህን ቡድንን የሰበሰቡት የአሁኑንና የወደፊቱን አገልግሎት እንዲያግዝ ነው። ለመጽሐፍ ቅዱሳዊና ነገረ መለኮታዊ አስተምህሮ ታማኝነት በእግዚአብሔር ላይ እየተደገፍን (2ጢሞቲዎስ 2፥2)፣ ስለ እነዚህ ስጦታው ስላላቸው መምህራን አመስጋኞች ነን።
ሲንክሌር ቢ. ፈርጉሰን

ዶ/ር ሲንክሌር ቢ. ፈርጉሰን የሊጎኔር ሚኒስትሪስ የትምህርት ባልደረባና በሪፎርምድ ቲዎሎጂካል ሲሚናሪ የስልታዊ ነገረ መለኮት ፕሮፌሰር ቻንስለር ነው። ቀደም ብሎ በኮሎምቢያ ደቡብ ካሮሊይና በሚገኘው ፈርስት ፕሪስባይቴሪያን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ዋና መጋቢ ሆኖ አገልግሏል። The Whole Christ, The Holy Spirit, In Christ Alone እና Devoted to God የሚሉትን ጨምሮ ከሃያ አራት መጻሕፍት በላይ ጽፏል።
ደብሊው. ሮበርት ጎድፍሬይ

ዶ/ር ደብሊው. ሮበርት ጎድፍሬይ በሊጎኔር ሚኒስትሪስ የትምህርት ባልደረባና በካሊፎርኒያ በሚገኘው ዌስትሚኒስቴር ሴሚናሪ የቀድሞ ፕሬዝዳንትና በጡረታ የተገለሉ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ፕሮፌሰር ናቸው። ስድስት ተከታታይ ክፍል ያለው የሊጎኔር የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ዳሰሳ ትምህርት ዋና መምህር ናቸው። God’s Pattern for Creation, Reformation Sketches, An Unexpected Journey እና Learning to Love the Psalms የሚሉትን ጨምሮ ብዙ መጻሕፍትን ጽፏል።
ጆኤል ኪም

ሬቨረንድ ጆኤል ኢ. ኪም የሊጎኔር ሚኒስትሪስ የትምህርት ባልደረባ ነው። እንዲሁም በካሊፎርኒያ ኢስኮንዲዶ በሚገኘው የዌስትሚኒስቴር ሴሚናሪ ካሊፎርኒያ (Westminster Seminary California) ፕሬዝዳንትና የአዲስ ኪዳን ረዳት ፕሮፌሰር ነው። በተጨማሪም፣ በፕሪስባይቴሪያን ቸርች ኢን አሜሪካ (Presbyterian Church in America) አስተማሪ ሽማግሌ ሲሆን በሚቺጋን ግራንድ ራፒድስ በሚገኘው ካልቪን ቲዎሎጂካል ሴሚናሪ (Calvin Theological Seminary) ዕጩ ዶክተር ነው። Everything in Christ በሚለው የሊጎኔር ተከታታይ ትምህርት ዋና አስተማሪ ሲሆን Romans: Nothing but Grace የተሠኘው መጽሐፍ ደራሲ ነው።
በርክ ፓርሰንስ

ዶ/ር በርክ ፓርሰንስ በፍሎሪዳ ሳንፎርድ በሚገኘው የሴንት አንድሪው ቻፕል ዋና መጋቢ፣ የሊጎኔር ሚኒስትሪስ የኅትመት ሥራ ዋና ኀላፊ፣ የቴብልቶክ መጽሔት አርታዒና የሊጎኔር ሚኒስትሪስ የትምህርት ባልደረባ ነው። በፕሪስባይቴሪያን ቸርች ኢን አሜሪካ የተሾመ አገልጋይና የቸርች ፕላንቲንግ ፌሎሺፕ (Church Planting Fellowship) ዳይሬክተር ነው። Why Do We Have Creeds? የሚለው መጽሐፍ ጸሓፊ፣ Assured by God እና John Calvin: A Heart for Devotion, Doctrine, and Doxology የተባሉት መጻሕፍት አርታዒ፣ A Little Book on the Christian Life by John Calvin የሚለው መጽሐፍ ተባባሪ ተርጓሚና ተባባሪ አርታዒ ነው። @BurkParsons በሚለው የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ይጽፋል።
ማይክል ሪቭስ

ዶ/ር ማይክል ሪቭስ የሊጎኔር ሚኒስትሪስ የትምህርት ባልደረባና በዩናይትድ ኪንግደም በሚገኘው የዩኒየን ስኩል ኦፍ ቲዎሎጂ (Union School of Theology) ፕሬዝዳንትና የነገረ መለኮት ፕሮፌሰር ነው። The Fear of the Lord የሚለውን ጨምሮ የሊጎኔር በርካታ ተከታታይ ትምህርቶች ዋና መምህር ነው። እንዲሁም፣ Preaching: A God-Centered Vision, Delighting in the Trinity እና Rejoice and Tremble የሚሉትን ጨምሮ የበርካታ መጻሕፍት ደራሲ ነው።
ዴሬክ ደብሊው. ኤች. ቶማስ

ዶ/ር ዴሬክ ደብሊው. ኤች. ቶማስ በኮሎምቢያ ደቡብ ካሮሊና በሚገኘው ፈርስት ፕሪስባይቴሪያን ቤተ ክርስቲያን ዋና መጋቢ ነው። ደግሞም በሪፎርምድ ቲኦሎጂካል ሴሚናሪ ውስጥ የስልታዊ ነገረ መለኮትና የመጋቢያዊ ነገረ መለኮት ፕሮፌሰር ቻንስለር ነው። የሊጎኔር ሚኒስትሪስ የትምህርት ባልደረባና How the Gospel Brings Us All the Way Home, Calvin’s Teaching on Job, የሚሉትንና ከዶ/ር ሲንክሌር ቢ. ፈርጉሰን ጋራ በመሆን የጻፉትን Ichthus: Jesus Christ, God’s Son, the Saviour የሚለውን ጨምሮ የብዙ መጻሕፍት ደራሲ ነው።
