የሚመራን መርሕ
የእውነት ክቡርነትና ቅድስና


አገልግሎታችንን የሚመራው ትልቁ መርሕ፣ የእውነት ክቡርነትና ቅድስና ነው። ሰዎችን ለማሳመን፣ ለመምከርና ለማበረታታት የምንፈልግ ቢሆንም ሐሰተኛ የጥፋተኛነት ስሜትን መጫንን፣ ወይም የአገልግሎቱን ጥቅሞችን ወይም አስፈላጊነትን አጋንኖ መናገርን የመሳሰሉ የማታለያ መንገዶችን በጥንቃቄ እናስወግዳለን። ስለዚህም ቀጥለው የተቀመጡትን መመዘኛዎች ለመከተል ቊርጠኞች ነን፦

  • የገንዘብ ቀውስ ቢገጥመን እንኳ “የቀውስ ጊዜ የርዳታ ጥሪዎችን” አናደርግም።
  • ለገንዘብ ርዳታና ለግዢ ሰዎችን አናስጨንቀም።
  • በሽያጭ ጊዜ የማታለያ ዘዴዎችን አንጠቀምም።
  • በምርቶቻችን ላይ ሐሰተኛ ቅናሽ የማድረግ ማታለያን አንጠቀምም።
  • ዋስትና ልንሰጥባቸው የማንችላቸውን ሐሰተኛ ጥቅሞችን ቃል አንገባም። 
  • በተበላሹ ምርቶች ላይ የሚቀርቡ የተማሪዎችን ቅሬታዎች ሳንከራከር እንቀበላለን። 
  • ከራሳችን አስፈልጎቶች ይልቅ በተማሪዎቻችን አስፈልጎቶች ላይ ለማተኰር እንጥራለን። 
  • ሁሉንም ተማሪዎቻችንን በአክብሮትና በትሕትና እንይዛለን።
  • ለግዢ ጥያቄዎችና ለርዳታ ፈጣን ምላሽ እንሰጣለን። 
  • ለተወሰነ ዐላማ የተመደቡ ገንዘቦችን ለተመደቡበት ትክክለኛ ዐላማ እንጠቀምባቸዋለን። 
  • ለተወሰነ ፕሮጀክት የተሰበሰበ ገንዘብ፣ ለዚያ ፕሮጀክት ብቻ እንጠቀመዋለን። 

ለጌታ ምላሽ እንደሚሰጥ ባለ ዐደራ፣ እነዚህን የሥነ ምግባር መርሖችን በሠራተኞቻችን ውስጥ ማዳበር ዐላማችን ነው፦


የማገልገል ልብ

  • የምናገለግላቸውን ሰዎች መረዳትና ከጠበቁት በላይ ማገልገል።
  • በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎችን ሕይወት ለማሻሻል መጽሐፍ ቅዱሳዊና ርቱዕ የሆኑ ምርቶችን ማሳደግ። 
  • በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ ሙያዊ አመራርና ግላዊ ዕድገትን መስጠት።

ለእውነተኛነት (ታማኝነት) ያለ ጥልቅ ፍላጎት

  • ሁሉንም መመዘኛዎችንና መስፈርቶችን ማሟላት።
  • የአገልግሎትና የምርቶችን ሁሉንም ገጽታ በቋሚነት በመገምገምና በማሻሻል ልዕቀትን ለማግኘት መጣር።
  • በግልጽነት፣ በታማኝነትና በእምነት አማካይነት ለጋራ የሚጠቅሙ ግንኙነቶችን ማሳደግ።

የታማኝነት አሻራ

  • ተቋሙን ለመጽሐፍ ቅዱስ ሕጸጽ አልቦነትና ለርቱዕ አስተምህሮ ማስገዛት።
  • ከዶ/ር አር. ሲ. ስፕሮል የሕይወት ዘመን አገልግሎት ጋራ ስምሙ የሆኑ ምርቶችንና አገልግሎቶችን መስጠት።
  • ሀብትን እንደ ባለ ዐደራ በአግባቡ መያዝን ማረጋገጥ።