
ተልእኳችን፣
ሰዎች ስለ እግዚአብሔርና ስለ
ቅድስናው ባላቸው ዕውቀት
እንዲያድጉ መርዳት ነው።
ዓለም ዐቀፋዊ ክርስቲያናዊ የደቀ መዝሙርነት ተቋም የሆነው ሊጎኔር ሚኒስትሪስ፣ በነገረ መለኮት ምሁሩ ዶ/ር አር. ሲ. ስፕሮል በ19 71 እ. ኤ. አ. የተመሠረተው፣ ክርስቲያኖች ምን እንደሚያምኑ፣ ለምን እንደሚያምኑ፣ እንዴት እንደሚኖሩትና እንዴት እንደሚያካፍሉት በግልጽ ማስረዳት እንዲችሉ ለማስታጠቅ ነው። የእግዚአብሔርን ቅድስና ማወጅ የሊጎኔር ማዕከላዊ ዐላማው ነው። ተልእኳችን፣ ጥልቅ ፍላጎታችንና ዐላማችን፣ ሰዎች ስለ እግዚአብሔርና ስለ ቅድስናው ባላቸው ዕውቀት እንዲያድጉ መርዳት ነው።
እግዚአብሔር ሕዝቡን በልባቸው መታደስ እንዲለወጡ ጠርቷቸዋል። ከባህል፣ ፍልስፍና፣ ዕቅብተ እምነት፣ ሥነ ምግባርና የቤተ ክርስቲያን ታሪክ አንጻር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ክብር ለማወጅ የምንፈልገውም ከዚህ የተነሣ ነው።
በድረ ገጻችን ላይ ትምህርቶችን፣ የጥናት መምሪያና የመልቲ ሚዲያ ይዘቶችን ወ.ዘ.ተ. ያገኛሉ። ይህም የእግዚአብሔርን ቅድስና በሙላቱ በተቻለ መጠን ለብዙ ሰዎች ለማወጅ፣ ለማስተማርና ለመመከት የሚሠራ አገልግሎት ነው። ይህም የእግዚአብሔርን ቅድስና በሙላቱ በተቻለ መጠን ለብዙ ሰዎች የማወጅ፣ የማስተማርና የመመከት ተልእኳችንን ለመፈጸም ነው።
